ለማህበረሰባችን ያለን ቁርጠኝነት

February 11, 2026

በ MCAEL ተልዕኮአችን ጎልማሳ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተማሪዎችን እና እነሱን የሚያገለግሉ ፕሮግራሞችን በመደገፍ ማህበረሰባችንን የማጠናከር ሂደት ላይ የተመሰረተ ነው። ከፍተኛ ፍርሃት እና እርግጠኛ ያለመሆን ሁኔታ በሚፈጠሩበት ጊዜያቶች ላይ፣ ስለ እሴቶቻችን እና ለምናገለግላቸው ሰዎች ስላለን ቁርጠኝነት በግልጽ መናገር ለእኛ አስፈላጊ ነው።


በሚኒሶታ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እየተከናወኑ ያሉትን የኢሚግሬሽን ህግ ማስከበር እርምጃዎችን የሚገልጹ እጅግ አሳሳቢ ሪፖርቶች፣ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ስደተኛ እና ስደተኛ ባልሆኑ ማህበረሰቦች ውስጥ ከፍተኛ ስጋትን መፍጠራቸው ግልጽ የሆነ ነገር ነው። ስለሆነም፣ በሜሪላንድ በተለይም በሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች በአካባቢያችን የኢሚግሬሽን ህግ የማስከበር እንቅስቃሴዎች ሊጨምሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ውስጥ መግባታቸው ተገቢ ነው። ይህ እርግጠኛ አለመሆን ሁኔታ የዕለት ተዕለት ኑሮን፣ የቤተሰብ መረጋጋትን፣ እንዲሁም ትምህርት እና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን የመፈለግ ፍላጎትን የሚጎዳ ፍርሃት፣ ጭንቀት እና የመጋለጥ ስሜትን ይፈጥራል።


የዚህን ሁኔታ ተፅዕኖ በየቀኑ የቅንጅት አጋሮቻችን፣ በአስተማሪዎች፣ በተማሪዎች፣ በበጎ ፈቃደኞች፣ እንዲሁም በጓደኞቻችን እና በቤተሰቦቻችን ዘንድ እናያለን፣ ይሰማናልም። ስደተኞች በጅምላ እና ባልተገባ ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ ወይም እንደ መንግስት ሸክም ተደርገው ሲቆጠሩ ጊዜ፣ ጉዳቱ ከቃላት ባለፈ የከፋ ይሆናል። ይህም መተማመንን ሊያናጋ፣ የማህበረሰቡን ደህንነት ሊሸረሽር እና የማህበረሰባችንን ማህበራዊ ትስስር ሊያዳክም ይችላል። ይህ እንዲሆን መፍቀድ የለብንም።


በታዋቂ የትምህርት ተቋማት፣ በመንግስት መሥሪያ ቤቶች እና በተለያዩ የፖሊሲ ድርጅቶች በሰፊ ጥናት የተደገፉ እና በደንብ የታወቁ እውነታዎችን በድጋሚ መግለጹ አስፈላጊ ነው። ሰነድ የሌላቸውን ጨምሮ ስደተኞች፣ በአሜሪካ ከተወለዱ ዜጎች ያነሰ ወንጀል እንደሚፈጽሙ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለአካባቢ፣ ለክልል እና ለፌዴራል ግብር እንደሚያበረክቱ፣ እንዲሁም በሥራ ኋይል እና አነስተኛ ንግዶችን በመፍጠር ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ በተደጋጋሚ ተረጋግጧል። እነዚህ ግኝቶች የግል አመለካከቶች አይደሉም፤ ለበርካታ አስርት ዓመታት በቆዩ አስተማማኝ ማስረጃዎች የተደገፉ ናቸው።


MCAEL በማህበረሰቦች እና በአካባቢ ተቋማት መካከል መተማመንን የሚያጎለብቱ፣ እንዲሁም ለህዝብ ደህንነት፣ ለጤና እና ለትምህርት ተደራሽነት አስፈላጊ የሆኑ ፖሊሲዎችን እና እሴቶችን ይደግፋል። እነዚህን መርሆች በሚገነዘብ እና እነሱን ለማስከበር በሚሰራ ካውንቲ ውስጥ በመኖራችን ደስተኞች ነን።


MCAEL ከተማሪዎቻችን፣ ከአጋሮቻችን፣ ከጎረቤቶቻችን፣ ከቤተሰቦቻችን እና ከማህበረሰባችን ጎን ይቆማል። ማንኛውም ሰው የኢሚግሬሽን ሁኔታው፣ የቋንቋ ችሎታው ወይም ብሔሩ ሳይለይ በፍትሃዊነት፣ በክብር፣ በርህራሄ እና በአክብሮት የመስተናገድ፣ እንዲሁም በቤቱ፣ በአካባቢው እና በዕለት ተዕለት ህይወቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ የመሰማት መብት እንዳለው እናረጋግጣለን። አዋቂ ተማሪዎችን እና እነሱን የሚያገለግሉ ፕሮግራሞችን ለመደገፍ፣ እንዲሁም በመላው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ጽናትን፣ መተማመንን እና እድሎችን ለማጠናከር ከአጋሮቻችን ጋር በጋራ ለመስራት ያለንን ቁርጠኝነት እናረጋግጣለን።

By Emma Starr May 12, 2026
With the correct spelling of funambulism (noun: the act of walking on a rope between two points elevated from the ground), the Montgomery College Spelling Bee team secured the Honeybee Trophy at MCAEL's 11th Annual Grown-Up Spelling Bee.  The competition was robust, with all five teams demonstrating impressive spelling skills. Along with Montgomery College, this year’s team line-up included Burness, Bethesda Magazine, GBCC NextExecs, and the Rockville Chamber of Commerce. Even the audience proved their prowess, spelling zenzizenzizenzic (noun: a number to the eighth power) during the Audience Spell, with a group of four audience members winning the prize (once they chased down the Bee, who had taken off with it). The event was buzzing with energy and good spirits. At the reception, guests posed in the photo booth and enjoyed refreshments while donning antennae headbands and bee sunglasses. This year’s People, Power, and Potential Award went to two women who were once English language learners themselves. Bibi Mohamed is the force behind the English language program at ISWA (the Islamic Society of the Washington Area). As Program Director, Bibi goes above and beyond to remove learning barriers for women, including childcare, housing and food insecurity, and transportation. Likewise, Milagro Flores, the CEO, Founder, and Executive Director of Mujer Fuerza y Coraje, is focused on women. She started her organization 16 years ago, when she realized that many women were facing the same challenges as she was – “difficulties communicating, limited job opportunities, and a deep fear of speaking with their children’s teachers. Many of us were also afraid to visit the doctor because we could not fully understand what was being said. We felt frustrated, isolated, and, at times, invisible.” Milagro’s words remind us of why adult English language learning is so vital. “We aren’t just supporting English classes,” MCAEL Executive Director Gerard Etienne explained in his remarks at the Spelling Bee. “Learning English is essential to workforce development, economic stability, healthcare access, safety, community connections, equity, mental health, and so much more. So, when adults learn English, the impact extends far beyond the individual – it strengthens and benefits the entire community.
By MCAEL March 26, 2026
Story written by Tamana Mehran
By Emma Starr February 18, 2026
MCAEL Executive Director Gerard Etienne sat down with Cheryl Hawkins of MMCTV’s Solutions to discuss all things MCAEL. Learn out about what MCAEL does, why it’s important, and Gerard’s own experiences as an English language learner. Watch the full 30-minute program by clicking the link above!